ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በመተባበር 15ኛውን የብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
የፓናል ውይይቱ “እኩልነትና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ ያለው፡፡
በፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ መንግስት ትርጓሜና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ ወርቁ አዳሙ ከህገ መንግስቱና ከፌደራል ስርአቱ አንጻር የዘንድሮውን መሪ ቃል ትርጓሜን በተመለከተ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
የዘንድሮው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በአዲስ አበባ የሚከበር ይሆናል፡፡
በፈቲያ አብደላ