Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል እየተወሰደ ስላለው ህግን የማስከበር እርምጃ ለአትላንቲክ ካውንስል አባላት ገለጻ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል እየተወሰደ ስላለው ህግን የማስከበር እርምጃ መቀመጫውን አሜሪካ ላደረገው አትላንቲክ ካውንስል የምርምርና የጥናት ተቋም አባላት ገለጻ ተደረገ፡፡

ገለጻውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚና ፖሊሲ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ እና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ ሰጥተዋል፡፡

በአፍሪካ ማዕከል በተሰጠው በዚህ ማብራሪያ እና ገለጻ ላይ ከአሜሪካ መንግስት የተወከሉ ባለስልጣናትን ጨምሮ የኮንግረስ አባላት ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የህወሓት ጁንታ በሰሜን እዝ ከፈጸመው ጥቃት እና ወታደራዊ ንብረቶችን ለመያዝ ያደረገውን ጥረት በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም መንግስት በትግራይ ክልል እየወሰደ ስላለው ህግ የማስከበር እርምጃ ገለጻ የተደረገ ሲሆን፥ ተሳታፊዎቹም ከዘመቻው ጋር ተያይዞ በንጹሃን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ከመቀነስ አንጻር ጥያቄ ቀርቧል፡፡

በተጨማሪም እየተወሰደ ያለው እርምጃ የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ፣ ከሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ጋር ስለሚደረገው ትብብር እና ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ከማስመለስ አንጻር እየደረገ ስላለው ጥረት ጥያቄ ተነስቶ ማብራሪ ተደርጓል፡፡

በወቅቱ በትግራይ ክልል እየተወሰደ ካለው ህግን የማስከበር እርምጃ ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ ውይይቶች እንዲደረጉም ሃሳብ ተነስቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.