Fana: At a Speed of Life!

በህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ላይ በኤሺያና ፓሲፊክ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችን ያሳተፈ ውይይት ተካሄደ፡፡

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኤሺያና ፓሲፊክ ሀገራት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ውይይቱ በዌቢናር የተካሄደ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በቻይና፣ አውስትራሊያ፣ ጃፓን፣ ኢንዶኔዥያ፣ ደቡብ ኮሪያ እና በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ውይይቱም በህዳሴ ግድብ የድርድር ሂደትና ህጋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን በህንድ ኒው ዴልሂ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በሚካሄደው የሶስትዮሽ ውይይት ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

የህዳሴ ግድብ ቴክኒካል ስራዎችና ህጋዊ ጉዳዮች በስፋት በውይይቱ ተዳሰዋል፡፡

ውይይቱን ያዘጋጀው በኒው ዴልሂ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሲሆን መድረኩን በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሸመ ቶጋ መርተውታል፡፡

የመወያያ አጀንዳውን በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ አለሙ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውሀ ሀብት ኢንጂነር ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ይልማ ስለሺ አቅርበዋል፡፡

በውይይቱም ሁሉም ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ግድቡ ከዳር እንዲደርስ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ተላልፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.