Fana: At a Speed of Life!

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች የመከላከያ ሰራዊት ለተቀዳጀው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች የመከላከያ ሰራዊት ለተቀዳጀው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላለፉ።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፥ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለመላው የኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ከሁሉም በላይ የጁንታው ቀንበር ለተሰበረላችሁ የትግራይ ህዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

በአንድነት ስሜት የተጀመረው የህግ የበላይነትን የማስከበር እና የሀገር ህልውና ዘመቻ በጀግናው የመከላከያ ድል አድራጊነት መጠናቀቁ አዲስ ምእራፍ ከፍቷል ብለዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርም “እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!! የሚል የደስታ መልእክቴን ሳስተላልፍላችሁ በታላቅ ኩራትና ደስታ ነው” ብለዋል

“ስግብግቡ ጁንታ እራሱ በቆፈረው ጉድጎድ እየቀበርነው ነው!! የክልላችንና የሃገራችን ህዝቦች የዘመናት የትግል ውጤት እውን ወደ መሆኑ ተቃርቧል” ሲሉም ገልፀዋል።

በቀጣይ መንግስት የሚወስደውን ወሳኝ እርምጃ በየጊዜው ለህዝቡ ይፋ ማድረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ ዛሬ በተቀዳጀነው ወሳኝ ድል በድጋሜ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በበኩላቸው፥ “ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ህግ የማስከበር ተግባር በታላቅ ወኔ እና እልህ የትግራይን ህዝብ ነጻ የማውጣት ዘመቻው በድል እያጠናቀቀ ይገኛል ነው ያሉት።

“ይህ ታላቅ ድል እንዲመዘገብ ለሀገራችን ክብር በጽናት ለታገለው ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ያለኝን ምስጋናና አክብሮት በድጋሚ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ” ብለዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.