Fana: At a Speed of Life!

አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የመከላከያ ሰራዊት ለተቀዳጀው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የመከላከያ ሰራዊት ለተቀዳጀው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላለፉ።

አፈ ጉባዔው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ “መላው ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ እንኳን ደስ አለን” ብለዋል።

“የትግራይ ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ላሳየው ድጋፍ እና ትብብር አክብሮታችን ከፍ ያለ ነው” ነው ሲሉም ገልፀዋል።

“መላው የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች እና አባላት ላደረጋችሁት ተጋድሎና መስዋዕትነት በራሴና በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስም እጅግ ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን” ብለዋል አቶ ታገሰ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.