ዓባይ ባንክ የ1 ሚሊየን ብር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት መሸጡን ገለፀ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓባይ ባንክ የ1 ሚሊየን ብር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት መሸጡን ገለፀ፡፡
ባንኩ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ መስራት ከጀመረ ወዲህ ደንበኖቹ የአውሮፕላን ትኬትን በቀላሉ በሞባይል ባንኪንግ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል።
ዓባይ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንግድ በዛሬው ዕለት በጋራ በሰጡት መግለጫ ቀላል እና ቀልጣፋ የሆነውን ይህን የትኬት ሽያጭ አገልግሎት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የአባይ ባንክ ከ250 ሺህ በላይ የኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ ደንበኞች እንዳሉት የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት በለጠ ዳኘው ተናግረዋል።
150 ሚሊየን ብር በመመደብ የባንኩን ዘመናዊ አሰራር ይበልጥ ለማዘመን እየተሰራ እንደሚገኝም ነው ያመለከቱት፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንግድ በሃገሪቱ ከሚገኙ ባንኮች ጋር በሞባይል ባንኪንግ ትኬት መሸጥ ከጀመረ ወዲህ 2 ቢሊየን ብር ሽያጭ ማስመዝገባ መቻሉን የአየር መንገዱ የገበያ ትስስር ዳይሬክተሩ አቶ ምህረትአብ ተክላይ ተናግረዋል።
በመለሰ ምትኩ