ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና እና ኢራን ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

By Tibebu Kebede

December 31, 2019

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና እና ኢራን በመካከላቸው ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ መስማማታቸው ተገልጿል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ሞሃመድ ጃቫድ ዛሪፍ በዛሬው ዕለት ከቻይና አቻቸው ዋንግ ይ ጋር በቤጂንግ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በሀገራቱ  መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም ቴህራን እና ቤጂንግ ያላቸውን የሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ አጋርነት ማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሞሃመድ ጃቫድ ዛሪፍ ሀገራቱ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸን ለማጠናከር እና በቅንጅት ለመስራት መስማማታቸው የሁለትዮሽ  ግንኙነታቸውን ለማሳደግ ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም ቤጂንግ እና ቴህራን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያድርጉትን ውይይት በቋሚነት ማስቀጠል ይገባቸዋል ነው ያሉት ።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ በበኩላቸው ሀገራቱ ያላቸውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል።

ምንጭ ፦https://www.presstv.com