ቴክ

በሊትር እስከ 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ የምትችል ተሸከርካሪ በኢትዮጵያዊ ወጣት ተሰራች

By Tibebu Kebede

December 31, 2019

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሊትር እስከ 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ የምትችል ተሸከርካሪ በኢትዮጵያዊ ወጣት መሰራቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ነዋሪ የሆነው ታዳጊ አጃዬ ማጆር ተሸከርካሪዋን ከወዳደቁ ብረቶች እንደሰራት ተነግሯል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባደረገለት ድጋፍ የተሰራችው  የባለ ሁለት እግር ተሸከርካሪ ሞተርን በመጠቀም የተሰራች ሲሆን ወደ ኋላ መሄድ እንድትችል ተደርጋ ተሻሽላ ተሰርታለች፡፡

አራት ኩንታል ክብደት ያላት ተሽከርካሪዋ እስከ 4 ሰዎች የመጫን አቅም ያላት ሲሆን በአንድ ሊትር እስከ 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ ትችላለች ተብሏል፡፡

ታዳጊው የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ መኪና መስራቱ ተገልጿል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለታዳጊው የተለያዩ ድጋፎችን  እንደሚያደርግ  ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡