Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ጁንታ በለውጥ ሃይሉ ላይ የእስር ትዕዛዝ በማውጣት የይስሙላ መንግስት ለማቋቋም ሲንቀሳቀስ ነበር – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓት ጁንታ በለውጥ ሃይሉ ላይ የእስር ትዕዛዝ በማውጣት የይስሙላ መንግስት ለማቋቋም ሲንቀሳቀስ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው የህውሓት ጁንታ በለውጥ ሃይሉ ላይ የእስር ትዕዛዝ በማውጣት የይስሙላ መንግስት ለማቋቋም ሲንቀሳቀስ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ህወሓት ላይ ለምን ቀድሞ እርምጃ አልተወሰደም የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው ጥያቄው ማሰብ በመፈለግና በማድረግ መካከል ያለን ልዩነት ካለመገንዘብ የመጣ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት የመንግስት ትዕግስት ማብዛቱ ዋጋ አላስከፈለንም ብለው ያስባሉ ለሚሉና ለመሰል ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በምላሻቸውም ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው አንድ ወር ቀደም ብሎ እና ወደ ስልጣን ከመጡበት ዕለት አንስቶ የገጠማቸውን ተግዳሮት አስረድተዋል፡፡

ከለውጡ ዋዜማ አንድ እና ሁለት ወር ገደማ ላይ በጁንታው ቡድን ከዓመታት በፊት ሲነሱ የነበሩ የህዝብ ጥያቄዎች የጁንታው ህውሓት ቡድን ከዚህ በፊት ህዝቡን በብዛት በማሰርና በማፈን ጥያቄዎቹን ለመቀልበስ ሲሞክር ነበር ብለዋል።

እንዲሁም ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው አስር ቀናት ቀደም ብሎ በለውጥ ሃይሉ ላይ የእስር ትዕዛዝ በማውጣት የይስሙላ መንግስት ለማቋቋም ሲንቀሳቀስ እንደነበርም አንስተዋል።

በተጨማሪም በለውጡ ዋዜማ የመፈንቅለ መንግስት ድርድሮች እንደነበሩም ነው ያነሱት፡፡

ከለውጡ በኋላም አንዱን ክልል ከአንዱ ክልል፣ በአንድ ክልል ውስጥ በሚኖሩ ሌሎች ብሄሮች መካከል ግጭቶችን አቀነባብረዋል ብለዋል፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ የሪፎርም ኃይሉ ከህወሓት ጋር በይቅርታ እና ያለፈውን በደል ባለማንሳት ለመሄድ መሰኑን አንስተው ነገር ግን ይህ እንደጠንካራ መንግስት ባህሪ ያለመታየቱን አመላክተዋል፡፡

የጥፋት ኃይሉም ህገመንግስታዊ ቅቡልነት በሌላቸው ድርጊቶቹ ሲቀጥል መንግስት የመከላከያ ኃይሉን የደህንነት ተቋማትን ሪፎርም ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ እርምጃ ለመግባት አለመዘግየታቸውን አንስተው የነበረውን ጠቅላላ ሁኔታ እና ተቋማዊ ብቃት ካለመረዳት የመነጨ ጥያቄ ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ቀድሞ እርምጃ ያልተወሰደው አንድን ነገር ከማድረግ በፊት ጥንቅቅ ያለ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ትንተና እና የሁኔታ ትንተና፤ ምን አይነት ዘመቻ በማካሄድ ስኬታማ እንሆናለን የሚለውን ማወቅ ስለሚያስፈልግ ነው ወደ እርምጃ ያልተገባው ብለዋል በምላሻቸው፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.