የሀገር ውስጥ ዜና

295 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

By Abrham Fekede

November 30, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 295 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግስትና የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት በትብብር መስራታቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ከስደት ተመላሽ ዜጎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡