Fana: At a Speed of Life!

ኢራን ባለፈው አርብ የተገደሉባትን የኒውክሌር ሊቋን ቀበረች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢራን ባለፈው አርብ የተገደሉባትን ከፍተኛ የኒውክሌር ተማራማሪ ሞሺን ፋክህሪዛዴህ በዛሬው ዕለት ቀብራለች።

ኢራን እያበለፀገች የሚገኘውን ኒውክሌር በግምባር ቀደምትነት እና በዋነኝነት ሲመሩ የነበሩት ሞሺን ፋክህሪዛዴህ ናቸው።

ሀገሪቱ በዘርፉ አሉኝ ከምትላቸው የኒውክሌር ባለሙያዎች መካከል አንዱ ለነበሩት ተመራማሪ መገደል እስራኤልን ተጠያቂ አድርጋለች።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የኢራን መከላከያ ሚኒስትር አሚር ሀታሚ ባደረጉት ንግግር ለሞሺን ፋክህሪዛዴህ ሞት የበቀል እርምጃ ሀገራቸው እንደምትወስድ እና የእርሳቸውን አሻራ አጠናክራ እንደምትቀጥል ቃል ገብተዋል።

ሌላኛው የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን ከግድያው ጀርባ በአካባቢው ያልነበረ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ጥቅም ላይ ውሏል ብለዋል።

እስራኤል በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት አስተያየት እስከአሁን ባትሰነዝርም ሞሺን ፋክህሪዛዴህ የኢራንን ሚስጥራዊ የኒውክሌር ስራ እንደሚከታተሉ እንደምታምን ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.