Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጨረር ህክምና መሳሪያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የመጀሪያው የጨረር ህክምና መሳሪያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ::
በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀደም ሲል የካንሰር የጨረር ህክምና ይሰጥ የነበረ ቢሆንም አሮጌ በመሆኑ የካንሰር ህመምተኞችን ለእንግልት ይዳረጉ እንደነበር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ዳዊት ወንድማገኘው ተናግረዋል፡፡
የጨረር ህክምና ለማግኘት ወረፋ በመጠበቅ ላይ እያሉም ህይወታቸው የሚያልፍ የካንስር ህመምተኞች ብዙ መሆናቸውን የጠቆሙት ዶክተር ዳዊት፥ አሁን የተመረቀው የካንሰር የጨረር ህክምና መሳሪያ ቀደም ሲል ይከሰቱ የነበሩ ችግሮች ይቀረፋሉ ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚዳንት ኘሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በኩላቸው የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሆስፒታሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ ትኩረት አድርገው መስራት አለባቸው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ የተመረቀውን የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጨምሮ በቀጣይ በጅማ፣ ጎንደር፣ ሀዋሳ እና ሀረር ሆስፒታሎች አገልግሎቱን ለመጀመር መታሰቡን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.