Fana: At a Speed of Life!

በአራት ወራት ውስጥ ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት አራት ወራት ጊዜ ውስጥ ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የግድቡ የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ የሕዝቡን የድጋፍ ተነሳሽነት መጨመሩ ተገልጿል።

የፅህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም የተጠቀሰው ገንዘብ የተሰባሰበው ከሐምሌ 2012 እስከ ጥቅምት 2013 ዓ.ም መሆኑን ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ በ2012 በጀት ዓመት 747 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታውሰዋል፡፡

ባለፈው ወርም 155 ሚሊዮን ብር በስጦታና በቦንድ ግዥ መሰባሰቡን ተናግረዋል።

ጽህፈት ቤቱ የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ለኅብረተሰቡ ያደረገው ቅስቀሳ ድጋፉ እንዲጠናከሮ ጉልህ አስተዋጽዖ ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን በማጠንከር ግድቡ እስከሚጠናቀቅ የሚያደርጉትን የገንዘብና የሞራል ድጋፍ እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አፍሪካዊያን የተፈጥሮ ፀጋን በራስ አቅም ማልማት እንደሚቻል የሚማሩበት ሲሆን ለሆቴል፣ ለቱሪዝምና መዝናኛ ዘርፍም ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.