የሀገር ውስጥ ዜና

የአሮጌው ብር የመገበያያ ጊዜ ከነገ ጀምሮ ያበቃል

By Abrham Fekede

November 30, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሮጌው ብር ኖት የመገበያያ ጊዜ ከነገ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃል።

የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል።

ባንኩ ከዚህ ቀደም ህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ከነገ ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም።

ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።

የብር ኖት ቅያሬው በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መወሰኑም አይዘነጋም።