Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ወዳጅነት ትኩረት እንደምትሰጥ ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ወዳጅነት ትኩረት እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

በኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ እና የአፍሪካ ህብረት ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ጆርጅ ኦሪና በኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር መለስ አለምን በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል፡፡

አምባሳደር ኦሪና ወደዚህ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ በመጀመሪያ ያነጋገሩት የኢትዮጵያን አምባሳደር መሆኑን ጠቅሰው፤ ሁለቱ ሀገራት የሚተባበሩባቸው መስኮች ፍሬያማ እንዲሆኑ በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡

አምባሳደር ኦሪና ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ወዳጅነት ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥ ገልፀዋል።

አምባሳደር መለስ አለም በበኩላቸው፥ የላሙ ወደብ፣ የሞያሌ የአንድ መስኮት ኬላ እንዲጠናቀቁ በማድረግ ወዳጅነቱን የላቀ ማድረግ እንደሚቻል ገልፀዋል

አዲስ የተሾሙት አምባሳደር ኦሪና ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የኬንያ ምክትል የሚሲዮን መሪ ነበሩ።

የኢትዮ-ኬንያ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እንደሚሰሩ ለአምባሳደር መለስ መግለፃቸውንም በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.