Fana: At a Speed of Life!

በከፊል ተቋርጦ የነበረው አራራት -ኮተቤ -ካራ የአስፓልት መንገድ ግንባታ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ ፣ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በከፊል ተቋርጦ የነበረው አራራት -ኮተቤ -ካራ የአስፓልት መንገድ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።
መንገዱ ከሶስት አመት በፊት የተጀመረ ቢሆንም ኮተቤ ካራ ደረስ ያለው ሁለተኛው ምዕራፍ በተቋራጭ አፈፃፀም ጉድለት መቋረጡ ይታወሳል፡፡
ፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት በቅርቡ በቅኝት ዘገባው÷ መንገዱ በተያዘለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ በነዋሪዎችና በአሽከርካሪዎች ላይ እያስከተለ ያለውን እንግልት ቃኝቶ መዘገቡ ይታወሳል።
ባለስልጣኑ የአፈፃፀም ችግር በነበረበት ተቋራጭ ላይ የማስቆም እርምጃን በመውሰድ በራስ ሃይል እንዲገነባ ወስኖ ወደ ስራ መግባቱን የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢያሱ ሰለሞን ለጣቢያችን አስታውቀዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም 5 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለውን መንገድ በበጀት አመቱ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ባለስልጣኑ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም መንገዱ ሲጠናቀቅ የትራፊክ ፍሰቱን እና አቅርቦቱን ከማስተካከሉም ባሻገር የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በማርታ ጌታቸው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.