Fana: At a Speed of Life!

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከትግራይ ተወላጆች ጋር በወቅታዊ ሃራዊ ጉዳይ ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከትግራይ ተወላጆች ጋር በወቅታዊ ሃራዊ ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙሰማ ጀማል እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ሃላፊ አቶ ይመር መሃመድ ተገኝተዋል።
በወቅቱም የአቃቂ ቃሊቲ የብልጽግና ፓርቲ ጽፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙሰማ ጀማል ÷ መንግስት በትግራይ ክልል እየሰራ ያለውን ህግ የማስከበር ስራ ምን ያህል እንደሰራ የሚያስገነዝቡ የተለያዩ ውይይቶች መካሄዳቸውንና ይህም ውይይት ለሁለተኛ ጊዜ መደረጉን ገልጸዋል።
በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በበኩላቸው÷ ከሆነ ህውሃት ከትግራይ ህዝብ ጋር የተለያዩ መሆናቸውንና ደግፈው ሲሰሩ የነበሩ አካላት ግን የትግራይ ህዝብን አይወክሉም ብለዋል ፡፡
መከላከያውም ቢሆን ከትግራይ ህዝብ ጋር የተዋለደ ቤተሰብ የመሰረተ ጭምር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መንግስት ህግ በማስከበር ውስጥ ህዝቡን በማስቀደም ህዝቡን ከጥቃት መጠበቁን እንደሚያደንቁም ተናግረዋል፡፡
መንግስት በትግራይ ክልል ህዝቡን የማረጋጋት ስራ ሊሰራ እንደሚገባ እና ህዝቡም የትግራይን ህዝብ ህውሓት ነው ብሎ በጥርጣሬ ከመፈረጅ ሊቆጠብ እንደሚገባ ጥያቄያቸውን አንስተዋል፡፡
የትግራይ ህዝብን ከህውሓት ጁንታው ቡድን ተለይቶ እንዲታይ በአዲስ አበባም ሆነ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መሰራቱን የአቃቂ ቃሊቲ የብልጽግና ፓርቲ ጽፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙሰማ ጀማል ተናግረዋል፡፡
በቅድስት ብርሀኑ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.