Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከኖርዌይና ኦስትሪያ አቻቸው ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ አቶ ደመቀ መኮንን ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪ ኤሪክሰንና እና ከኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ሻለንበርግ ጋር ዛሬ በስልክ ተወያይተዋል።
አቶ ደመቀ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ጋር ባደረጉት ውይይትም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለጻ አድርገዋል።
በዚህም መንግስት በትግራይ ክልል እያከናወነ ያለው የህግ ማስከበር ስራ እና ለዜጎች እያደረገ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍ አብራርተዋል፡፡
አቶ ደመቀ አያይዘውም ትግራይ ከጁንታው አገዛዝ ሙሉ በሙሉ ነፃ መውጣቷን ጠቁመው አሁን መንግስት የፈረሱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት እና የተሰደዱ ዜጎችን ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የማረጋገጥ ስራ ይሰራል ብለዋል።
መንግስት ሁል ጊዜ ለድርድር በሩ ክፍት ቢሆንም ነገር ግን ከወንጀለኞች ጋር ግን አይደለም ብለዋል አቶ ደመቀ።
ሆኖም በበርካታ ጉዳዮች ላይም መንግስት ከትግራይ የሽግግር መንግስት እና ከሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መነጋገሩን እንደሚቀጥልም አስረድተዋል።
በሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ሥጋቶችን ለመመለስም የፌዴራል መንግሥት ከሚመለከታቸው አካላትና ከዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የተውጣጣ ልዑክ በመሬት ላይ ያሉ ሰብዓዊ ፍላጎቶችን ለመገምገም መላኩን ተናግረዋል ፡፡
መንግስት የሚያደርገውን ጥረቶች ለሚደግፉ ዓለም አቀፍ አጋር አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ ደመቀ አያይዘውምወደ ሱዳን የተሰደዱ ሰዎችን አስመልክቶም መንግስት በፈቃደኝነት ወደ አገራቸው የሚመለሱትን ለመቀበል አራት መጠለያዎች ማቋቋሙን ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት ሰብአዊ ጉዳዮችን ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.