Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአስር ዓመት ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአስር ዓመት ውስጥ የአፍርካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማት አሸናፊ መሆኑ ተገለጸ።

ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አስቸጋሪ በሆነው የአፍሪካ ቀጣና እና ፈታኝ በሆነ ወቅት ባስመዘገበው ድንቅ ስኬት መሸለሙም ታውቋል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እውነተኛው የፓን አፍሪካኒዝም ምሳሌ በመባል አድናቆት ተችሮታል።

አየር መንገዱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ያስመዘገበው ትርፍም የስኬት መንገዱን ያሳየ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ከዚህ በተጨማሪም አየር መንገዱ እንደ ቻይናና ዱባይ ባሉ ከፍተኛ የንግድ፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች ላይ የሚሰጠው አገልግሎት ተመራጭ እንዳደረገውም ተጠቁሟል።

በአየር መንገዱ እየተካሄደ ያለው የማስፋፊያ ፕሮጀክትና በምቾት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ዘመናዊ አውሮፕላኖቹ አየር መንገዱን ከአፍሪካ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ እንዳደረገውም ፍላይት ግሎባል መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.