Fana: At a Speed of Life!

ብሪታንያ ፋይዘር የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሪታንያ ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተሰኙ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፍቃድ ሰጠች፡፡

ብሪታንያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ስትሰጥ ከምዕራባውያን ሀገራት መካከል የመጀመሪያዋ ያደርጋታል ነው የተባለው፡፡

ይህ ክትባት 95 በመቶ ፈዋሽነቱን የተረጋገጠ መሆኑ የብሪታንያ የበሽታ ተቆጣጣሪዎች ገልጸዋል፡፡

ክትባቱ በቀጣዩ ሳምንት ለብሪታኒያውያን ይሰጣልም ነው የተባለው፡፡

የብሪታያ መንግስት 20 ሚሊየን ሰዎችን መከተብ የሚችል 40 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት ማዘዙ የተሰማ ሲሆን 10 ሚሊየን ያህሉን በቀናት ውስጥ እንደሚረከብ ይጠበቃል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ አንድ ክትባት ከሐሳብ ጀምሮ ወደ ተግባር እስከሚገባ ዓመታት የሚወስድ ሲሆን አሁን ይፋ የሆነው ክትባት በ10 ወራት ውስጥ በመጠናቀቁ ታሪካዊ ነው ተብሎለታል፡፡

ክትባቱን በመጀመሪያ ዙር የጤና ባለሙያዎችና ዕድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ የሆናቸው የሚወስዱ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆናቸው እና የጤና እክል ላለባቸው ወጣቶች ይሰጣል ተብሏል፡፡

እንዲሁም በቅርቡ የሞደርናና ሌሎች የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችም ፍቃድ ሊያገኙ እንደሚችሉ ተሰምቷል፡፡

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

በአብርሃም ፈቀደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.