Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል በሚገኙ ባንኮች ሒሳብ የከፈቱ እና ከትግራይ ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት አካባቢ ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል በሚገኙ ባንኮች ሒሳብ የከፈቱ እና ከትግራይ ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት አካባቢ ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መፈቀዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በወንጀል ተጠርጥረው ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ ከተደረገው ደንበኞች በስተቀር በትግራይ ክልል በሚገኙ ባንኮች ሒሳብ የከፈቱ እና ከትግራይ ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት አካባቢ ሒሳባቸውን ከዛሬ ጀምሮ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መፈቀዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በትግራይ ክልል እየተከናወነ ባለው የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የፀጥታው ሁኔታ ለባንኮች አመቺ በሆነባቸው ከተሞች ባንኮች ተከፍተው ሥራ እንዲጀምሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው ጋር እየሠራ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

የፀጥታው ሁኔታ አመቺ ባልሆነባቸው ከተሞች ደግሞ ባንኮች ተዘግተው የሚቆዩ መሆኑን ነው የገለጸው።

በትግራይ እየተካሄደ ባለው የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ምክንያት የፀጥታው እና የኔትወርክ ሁኔታ እስኪሻሻል ባንኮች ተዘግተው እንዲቆዩ መወሰኑ ይታወሳል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.