Fana: At a Speed of Life!

የቴሌኮም አገልግሎት በአላማጣ ሙሉ ለሙሉ ሲጀምር በሌሎች አካባቢዎች በከፊል ወደ ስራ ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቴሌሎም አገልግሎት በአላማጣ ከተማ ሙሉ ለሙሉ ሲጀምር በሌሎች አካባቢዎች በከፊል መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

በከፊል የተጀመረባቸው አካባቢዎች ዳንሻ፣ በተርካን፣ ሁመራ፣ ሽራሮ፣ ማይጸምሪ እና ማይካድራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ላይ ያጋጠሙ ጉዳቶችን ለመጠገንና መልሶ በማቋቋም እንዲሁም አማራጭ የኃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም አገልግሎት መጀመሩ ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በተቀሩት የትግራይ አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር የተጎዱ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን ለማስጠገን መልሶ ለማቋቋም እንዲሁም መደበኛ የኃይል አቅርቦት ለማግኘት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑንም ገልጿል፡፡

አማራጭ የኃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀው፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.