የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ፖሊስ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን መቐለ ገባ

By Tibebu Kebede

December 02, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን መቐለ ከተማ መግባቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

መቐለ የገባው ቡድን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት የጁንታውን ተፈላጊ ወንጀለኛ ቡድን ማደን ጀምሯል ተብሏል።

የኮማንዶ ቡድኑ በከተማዋ በሚያደርጋቸው አሰሳዎችና የተለያዩ ዘመቻዎች እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ቡድኑ የሚገኙ ውጤቶች በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!