Fana: At a Speed of Life!

በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ ከጣሊያን ሴኔት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ ከጣሊያን ሴኔት ፕሬዚዳንት ማሪያ ኤሊዛቤታ ካሴላቲ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።

በውይይቱ አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡

የጣሊያን ሴኔት ፕሬዚዳንት ማሪያ ካሴላቲ በበኩላቸው ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የጠበቀ ወዳጅነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም በሃገራቱ መካከል የነበሩ ዘርፈ ብዙ ትብብሮች እና ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ወቅታዊ ችግር በተመለከተ በቅርበት እየተከታተሉት መሆኑን እና ጉዳዩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፈቱታል የሚል እምነት እንዳላቸው መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.