አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለካናዳ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ከሰሃራ በታች ምክትል ሚኒስትር ገለጻ አደረጉ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለካናዳ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ከሰሃራ በታች ምክትል ሚኒስትር ማላ ካሃና ገለጻ አደረጉ፡፡
አምባሳደር ናሲሴ በወቅቱም በመንግስት በትግራይ ክልል ስለወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ አብራርተዋል።
በማብራሪያቸውም ዘመቻው የሃገሪቱን ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ለመታደግ እና አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም አምባሳደሯ መንግስት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት ከአጋሮች ጋር ለመስራት ቁርጠኛ እና ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል ፡፡
በካናዳ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ከሰሃራ በታች ምክትል ሚኒስትር ማላ ካሃና በበኩላቸው÷ በአምባሳደር ናሲሴ ለተደረገላቸው ማብራሪያ አመስግነው፥ የካናዳ መንግስት ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጎን ይቆማል ብለዋል፡፡
የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋምና የፈረሱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት በኩል የካናዳ መንግስት የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!