በደሴ በ591 ሚሊየን ብር የአስፓልት መንገድ ስራ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደሴ ከተማ በ591 ሚሊየን ብር ወጪ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ስራ ተጀመረ።
የከተማው ቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ መከተ ዘውዱ የመንገድ ግንባታ ስራውን አስጀምረዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ወጪ የሚገነባው የ7 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ብለዋል።
የአስፓልት መንገድ ግንባታው ከመናፈሻ ተቋም፣ ከኮሽን በር ገራዶ፣ ከወሎ ሆቴል ከንቲባ ጽህፈት ቤት፣ ከፒያሳ መድሃኒአለም፣ ከደሴ ሪፈራል ሆስፒታል በሮቢት ዶልፊን አካባቢዎችን እንደሚያካልልም ተናግረዋል፡፡
መንገዱ ከዚህ ቀደም በጠጠርና አስፓልት ደረጃ ተሰርቶ በረጅም ጊዜ አገልግሎት የፈራረሰ በመሆኑ በአዲስ መልክ የአስፓልት ግንባታው መጀመሩን አስታውቀዋል።
መንገዱ ይሰራል እየተባለ በተደጋጋሚ ለህዝብ ቃል ቢገባም በተለያዩ ምክንያቶች ባለመሳካቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ መቆየቱን አስታውሰው “የለውጡ አመራር ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ጥረት ግንባታው ሊጀመር ችሏል” ብለዋል ።
የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አስማማው አለማየሁ የመንገድ ግንባታ ስራው በውሉ መሰረት በተያዘለት ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ እንደሚደረግ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!