Fana: At a Speed of Life!

15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በአዲስ አበባ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)15ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ተከበረ።
በዓሉ “እኩልነትና ህብረ ብሄራዊነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ነው ተከብሮ የዋለው።
በበዓሉ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ከዚህ በኋላ እውነተኛ ፌደራሊዝምን ለመተግበር በትክክለኛ እና እውነተኛ መንገድ እንጂ በሀሰት እና በማታለያ መንገድ አንጓዝም ብለዋል።
ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን ለበርካታ ዓመታት በፌደራዝም ስም የበርካቶችን ደም አፍስሷል ያሉት አቶ ሽመልስ፥ ከዚህ በኋላ ግን በእውነተኛ እና ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች አሳታፊ መንገድ ውጪ መጓዝ አይቻልም ሲሉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የእኩልነት፣ የዴሞክራሲ፣ የነፃነት እና የወንድማማችነት መንገድ ነው የሚገባት ያሉት አቶ ሽመልስ፤ የህቤር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ስናከብርም ይህነን ባገናዘበ መልኩ መሆን ይገባልም ብለዋል።
“ቀሪ የህዝብ ጥያቄዎችንም ዴሞክራሲያዊ መሆነ መንገድ ለመመለስ ለሁሉም ተስማሚ የሆነ እውነተኛ እና ሁሉንም በእኩልነት የሚያገለግል የፌደራሊዝም ስርዓት እየገነባን ነው” ሲሉም ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

ለተንቀሳቃሽ ምስሎች  የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.