Fana: At a Speed of Life!

የብሄር ብሄረሰቦች አውደ ርዕይ የመክፈቻ ስነ ስርአት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ15ኛው የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት የብሄር ብሄረሰቦች አውደ ርዕይ የመክፈቻ ስነስርአት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄደ፡፡

“ህብረ ብሔራዊ አንድነትና እኩልነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ቀኑ የሚከበር ሲሆን የብሔር ብሔረሰቦችን አንድነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ጉዳዮች በአውደ ርዕዩ ላይ ቀርበዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ አውደ-ርዕዩ የኢትዮጵያ ህዝቦችን ባህል፣ ታሪክና ቅርስ በአንድ መድረክ ለማስተዋወቅ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ ሃገር መሆኗን አስታውሰው፤ በርካታ የጋራ የሆኑ ማንነቶች እንዳላቸውም አውስተዋል፡፡

ህብረ ብሔራዊ ሃገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ለብሔሮችና ብሔረሰቦች እኩል እድል መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፥ ህገ መንግስቱ ህዝቦች ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውንና ታሪካቸውን ለማሳደግ ቢደነግግም በበቂ መጠን እንዳልተሰራበት ጠቅሰዋል።

ባለፉት ዓመታት በተከበሩ በዓላት ብሔር ብሔረሰቦችን በማቀራረብና ባሕላቸውን በማስተዋወቅ በኩል የተገኙ ውጤቶች መኖራቸውን አስታውሰው፤ “የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሕገ መንግስቱና በፌደራል ስርዓቱ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ አልተደረገም” ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የኩሩና ድንቅ ህዝቦች እናት መሆኗን አንስተዋል።

ለዚህ አንዱ ምስክር የአድዋ ድል መሆኑን ጠቅሰው ለኢትዮጵያ ብልጽግና በተባበረ ክንድ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ጠላት ሆኖ ይሰራ የነበረው የህወሓት ጁንታ በመከላከያ ሰራዊት ድል በተደረገበት ማግስት በዓሉ መከበሩ ልዩ ያደርገዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.