Fana: At a Speed of Life!

በኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ የሚነሳው ቅሬታ መቀረፍ እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመብራት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚያነሳው ቅሬታ እና እሮሮ መቅረፍ እንዳለበት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሀብት፣ መስኖ እና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ህዝቡ አሳሰበ።

ቋሚ ኮሚቴው ይህን ያሳሰበው፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ተደራሽነት እና የአገልግሎት አሰጣጡን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ምእራብ፣ ምስራቅ እና ሰሜን ሪጅኖች በተመረጡ ስድስት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማዕከላት የመስክ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ነው።

ኮሚቴው ተዘዋውሮ ጉብኝት ባደረገባቸው እንዳንድ ማዕከላት ደንበኞችን በአነጋገረበት ወቅት የመብራት ካርድ ክፍያ ለመፈጸም ሲስተም የለም በሚል ምክንያት በአላስፈላጊ ሰልፍ ጊዜያቸውን እያባከኑ እንደሆነ እና የተቋሙ 905 የጥሪ ማዕከል የማይነሳ መሆኑን ተገንዝቧል።

የኤሌክትሪክ አገልግሎት በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ብልሽት በሚከሰትበት ወቅት የተቋሙ ባለሙያዎች ጥገና ለማድረግ የሚዘገዩ እንደሆነ እና ማህበረሰቡ የተቋሙን የጥገና ባለሙያዎች በገንዘብ ለመደራደር የሚገደዱ እንደሆነ የቋሚ ኮሚቴው አባላት መረጃዎች እንዳሏቸው አመላክተዋል።

ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲፈፅሙ ታስቦ በንግድ ባንክ ትስስር መፈጠሩ በተቋሙ ከታዩ መሰረታዊ ለውጦች አንዱ እንደሆነ የተገነዘበው ቋሚ ኮሚቴው፤ ቴክኖሎጂውን ከደንበኞች ጋር ከማላመድ እና ግንዛቤ ከመፍጠር አንፃር አሁንም የአቅም ውስንነቶች መኖራቸውን ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ በበኩላቸው፥ ቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ ባደረገባቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማዕከላት በጥንካሬ እና በክፍተት የታዩ  ጥቦች እንደ ግብዓት የሚወሰዱ መሆኑን ገልጸው፣ ተቋሙን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማደራጀት ሁለንተናዊ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የሚከሰተውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጥ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በአዲስ አበባ ከተማ ፖሎችን ለመቀየር ስምንት ቢሊየን ብር ተመዶቦ ስራው እየተከናወነ እንደሆነም በውይይቱ መገለፁን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.