አቃቤ ህግ አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ያቀረበውን ሁለተኛ ክስ አሻሻለ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ጠቅሎይ አቃቤ ህግ አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ያቀረበውን ሁለተኛ ክስ አሻሻለ።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎት አቃቤ ሀግ ከዚህ በፊት ያቀረበው ክስ ተጣምሮ በመሆኑ እና ግልፅ ባለመሆኑ ተሻሽሎ አንዲቀርብ ለዛሬ በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ነው ክሱ ተሻሽሎ የቀረበው።
ከዚህ በፊት አቃቤ ህግ የወንጀል ህግ 238/1B እና 256ን አጣምሮ አቅርቧል በሚል ነው እንዲያሻሽል የታዘዘው።
በዚሁ መሰረትም አቶ ልደቱ አያሌው በወንጀል ህግ 238 ንኡስ አንቀፅ 1B በመተላለፍ ህገ መንግስት እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ የተለያዩ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነዶችን አዘጋጅተው እና በፍተሻም የተያዘባቸው ነው ሲል አቃቤ ሀግ ክሱን ነጥሎ እና ግልፅ በማድረግ አሻሽሎ አቅርቧል።
ክሱን የተቀበለው ፍርድ ቤቱ የተሻሻለውን ክስን በችሎት አንብቧል።
የአቶ ልደቱ ጠበቆችም በተሻሻለው ክስ ላይ መቃወሚያቸውን በጽሁፍ እናቅርብ ሲሉ የጠየቁ ሲሆን፥ በጥያቄያቸው መሰረት መቃወሚያቸውን ለመመልከት ለታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠረቶ ተሰጥቷል።
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!