Fana: At a Speed of Life!

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት የሚገልጽ ዝግጅት አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 25፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነትና ድጋፍ የሚገልጽ ዝግጅት አካሂደዋል።
የመከላከያ ሰራዊት በከሃዲውና ጽንፈኛው ህወሓት ቡድን የተቃጣበትን ጥቃት መክቶ በፍጥነት ኢትዮጵያን ወደ ድል ብስራት በማሸጋገሩ ያላቸውን ደስታም ገልጸዋል።
ለዚህ የሀገር መከታ መከላከያ ሃይል ድጋፍ ለማድረግና በጽንፈኛው ህወሓት እርጥባን ተከፋዮች የሚነዛውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳን ለማክሸፍ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።
ዝግጅቱ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አስተባባሪነት የተካሄደ መሆኑን በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.