Fana: At a Speed of Life!

ም/ከንቲባ አዳነች ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በ1 ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለውን የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ በ1 ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለውን የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል የግንባታ ሥራ ጎበኙ።
ወይዘሮ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የገበያ ማዕከሉ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እተየገነባ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ የሚገነቡት የመገበያያ ሼዶች ከ70 በመቶ በላይ መጠናቀቃቸውንም ነው የጠቀሱት።
በመጀመሪያው ምዕራፍ ከሚገነቡት 14 ሼዶች ውስጥ 588ቱ የመገበያያ ሱቆች እንዳሉትም አንስተዋል።
ይህንን ስራ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሌት ተቀን ለሰሩት ተቋራጩ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና አሰሪውን የአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ቢሮን አመስግነዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.