Fana: At a Speed of Life!

የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮጀክት 2009 ዓ.ም ላይ ሲጀምር በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙ የከተማ ዜጎችን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥን ዓላማው አድርጎ ነው፡፡

ውጤታማነቱም በኢትዮጵያ መንግስትና በዓለም ባንክ መረጋገጡ ነው የተጠቀሰው፡፡

ፕሮጀክቱን በበላይነት የሚመራው የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ ሰሞኑን በፕሮጀክቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ውሳኔ ከተሰጠባቸው ዓበይት ጉዳዮች መካከል የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም የ2013 ዓ.ም በጀት ማጽደቅ አንዱ መሆኑን ከፌዴራል የከተሞች የስራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

እንዲሁም የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክትን የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮጀክት አካል ማድረግ፣ የዩኒሴፍ እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም የድጋፍ በጀት የ2013 የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት በጀት አካል እንዲሆን ማጽደቅ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.