Fana: At a Speed of Life!

ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውን የደብረታቦር እና ሀረማያ ዩኒቨርሲቲዎች ተናገሩ።
በቀጣይ ሳምንት ተመራቂ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ያደረጉት የደብረታቦር እና ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች የኮቪድ 19 ወረርሽኝን መከላከል የሚያስችሉ ዝግጅቶችን ማድረጋቸውን ለፋና ብሮድካድስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
ታህሳስ 1 እና 2 ቀን 2013 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎቹን ለመቀበል ጥሪ ያደረገው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዳይስተጓጎል ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው ተናግረዋል።
ዝግጅቱም ከአካባቢው ህብረተሰብ፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከወጣቶች፣ ከፀጥታ አካላት እና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን መደረጉን ገልፀዋል፡፡
ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎቹን የሚቀበለው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲም የመማር ማስተማር ሂደቱን ሊያደናቅፉ የሚችሉ አሉታዊ ነገሮች እንዳይኖሩ ከበርካታ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለምሸት ተሾመ ተናግረዋል።
አባ ገዳዎችን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እና የፀጥታ አካላት ለዚሁ ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
በሌላ በኩል ከገፅ ለገፅ ትምህርት በተጨማሪ የኦንላይን ትምህርትን በመስጠት የባከኑ ወራቶችን ለማካካስ ይሰራል ብለዋል፡፡
ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ገበታቸው ሲመጡ ለሰላም ዘብ የሚቆሙ፣ አላማቸውን ለማሳካት ብቻ መሆን እንዳለበት እንዲሁም የሰላም ፀር ለሆኑ አካላት አጀንዳ አስፈፃሚ ከመሆን እንዲጠነቀቁም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የደብረታቦር እና ሀረማያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸው በሁለት ወር ውስጥ ትምህርታቸውን እንዲያጠናቅቁ እና እንዲመረቁ እንደሚያደርጉ ነው ያስታወቁት።
በዙፋን ካሳሁን

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.