Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሚዲያ ሚና በቀውስ ጊዜ በሚል ርዕስ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሚዲያ ሚና በቀውስ ጊዜ በሚል ርዕስ በሰላም ሚኒስቴር አመቻችነት የበይነ መረብ ውይይት ተካሄደ።

ውይይቱን የከፈቱት የሰላም ሚኒሰትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም ዓቀፍ እና የሀገር ውስጥ የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት መካሄዱ እጅግ ጠቃሚ ነው ብለዋል።

የሚዲያ ባለሙያዎች የሚዲያን ሰላም የማስፈንም ሆነ ጥፋት የማስከተል አቅም በሚገባ ተገንዝበው በተለይም በአስቸጋሪ ወቅቶች ጊዜ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ትክክለኛ መረጃን የማቀበል ስራቸውን በአግባቡ መወጣታቸው ለሰላም ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክተዋል።

በተጨማሪም ሚኒስትሯ ለተሳታፊዎቹ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ህግ የማስከበር ሂደትና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በውይይቱ ፕሮፌሰር አን-ፊትስ ጄራለድ ከካናዳ፣ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን አቶ ድጋፌ ደባልቄ ከካናዳ እንዲሁም ወይዘሮ ቬነስ ናራያን ከለንደን በርዕሱ ዙሪያ ሀሳባቸውንና ልምዳቸውን ለተሳታፊዎች ማካፈላቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.