Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር የበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ላይ ሬና ገላኒ፣ በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት የሰብዓዊ ድጋፍ ዳይሬክተር፣ ዶክተር ካትሪን ሶዚ፣ በተባበሩት መንግስታት አስተባባሪና የሰብዓዊ ድጋፍ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተካፍለዋል።

ሚኒስትሯ በሰሜናዊ የኢትዮጵያ ክፍል በተካሄደው የህግ ማስከበር ሂደት እንዲሁም ከወታደራዊ ህግ የማስከበር ሂደት ቀድሞ ሰላምን በሰለጠነ መልኩ በውይይት ለማምጣት ስለተሄደው ረጅም ርቀት ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

በሰላም ማስከበር ሂደቱም ንጹሃን እንዳይጎዱና መሰረተ ልማት እንዳይፈርስ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ የተሞላበት ዘመቻ እንደተካሄደ አስረድተዋል።

ሬና ገላኒ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው በኢትዮጵያ መንግስት ንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ የተደረገውን ጥረት አድንቀዋል።

በመጨረሻም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሁልጊዜውም ሰብዓዊና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን ከመንግስት ጋር በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.