የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮ ሱዳን ወታደራዊ የጋራ የጥምር ኮሚቴ ውይይት አካሄደ

By Abrham Fekede

December 04, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ 22ኛ ንስር ክፍለጦር የ3ኛ ብርጌድ 3ኛ ሻለቃ እና የፌደራል ፖሊስ አመራር ፣  ከሱዳን 13ኛ ክፍለጦር 14ኛ ብርጌድ 9ኛ ሻለቃ አመራር የጋራ ጥምር ወታደራዊ ኮሚቴ  በሁለቱ ሃገራት ድንበር አካባቢ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ መሰረት ያደረገ ውይይት አካሂዷል ።

የ3ኛ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሰለሞን አፈራ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ፤ የኢትዮ ሱዳን ግንኙነት ለበርካታ አመታት የቆየና የሁለቱ ሃገራት የትብብር ስምምነት ለሰላም ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በቀጣይነትም ሁለቱ ሀገራት በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ አመላክተዋል ።

በሱዳን የ9ኛ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል መሀመድ አደም ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሰላምና ደህንነት ዙሪያ በጋራ እየሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል ።

ሁለቱ ሃገራት የመረጃ ልውውጥ በማድረግ፣ በድንበር አካባቢ የጋራ ቅኝት ስራዎች በማከናወን፣ ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውርን እና ኮንትሮባንድ ንግድን መቆጣጠር የሚያስችሉ የጋራ ስራዎች ማከናወናቸውንም ተናግረዋል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን