Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ስዊድን ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ትስስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከስዊድኑ የልማት ትብብር ምክትል ሚኒስትር ፔር ኡልሰን ፍሪዝ ጋር በስልክ ተወያዩ።
በውይይታቸው በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደት ውስጥ ከመገባቱ አስቀድሞ ሰላምን በምክክር ለማስፈን የተሄደበትን ረጅም ርቀት አስረድተዋል።
በተጨማሪም ህግ የማስከበሩ ሂደት ሰላማዊ ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው በከፍተኛ ጥንቃቄ መካሄዱን ተናግረዋል።
የስዊድኑ ምክትል ሚኒስትር በበኩላቸው በሁለቱ ሃገራት መካከል የቆየው የእህትማማችነት ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ባለው ሁኔታ የተጎዱ ዜጎችን መልሶ የማቋቋምና መሰረተ ልማትን መልሶ የመገንባት ርብርብን ለመደገፍ ከኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ጎን እንደሆኑ ማረጋገጣቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.