የሀገር ውስጥ ዜና

በአፋር ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 26 ቀን ጀምሮ ይሰጣል

By Feven Bishaw

December 04, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 26 እስከ 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ ሁመድ በክልሉ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተላልፎ የነበረው የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተጠቀሰው ቀን እንደሚሰጥ ገልፀው÷ ተማሪዎች በቀሪ ጊዚያት እንዲዘጋጁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፈተናውን የሚወስዱት በ271 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ 7 ሺህ 984 ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥም 4 ሺህ 837 የሚሆኑት ወንዶች፣ 3 ሺህ 147 ደግሞ ሴት ተፈታኞች መሆናቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡