የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ድሪባ ኩማ ለስዊድን እና አካባቢው ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች በትግራይ ክልል ስለተወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ገለጻ አደረጉ

By Tibebu Kebede

December 05, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ድሪባ ኩማ ለአካባቢው ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች መንግስት በትግራይ ክልል ስለወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ገለጻ አደረጉ፡፡

አምባሳደር ድሪባ ገለጻውን ለስዊድን፣ ኖርዌይ እና ዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፥ የህወሓት ወንጀለኛ ቡድን በፈጸመው ህገ ወጥ ድርጊት የተነሳ መንግስት ህግ ለማስከበር መገደዱን አብራርተዋል፡፡

አያይዘውም የህወሓት ቡድን ህገ መንግስቱን በጣሰ መልኩ በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙንም አስረድተዋል፡፡

በመንግስት የተወሰደው ህግን የማስከበር ዘመቻም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማስከበር አንጻር አስፈላጊና ወሳኝ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

የህግ የማስከበር ዘመቻው የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ መጠናቀቁንም አውስተዋል፡፡

የስራ ሃላፊዎቹም የትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዲተባበሩ ጥሪ ማቅረባቸውን በስዊድን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!