የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከመልቲቾይስ የቦርድ ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

December 05, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከመልቲቾይስ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ኢምቲያዝ ፓቴል ጋር ተወያዩ፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች የጋራ እሴቶችን ከማስተዋወቅ አንጻር ያላቸውን ሚና በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም መሰል ድርጅቶች መጪዉን ትውልድ ከመቅረጽ አኳያ ስላላቸው ሚና ገለጻ ማድረጋቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መልቲቾይስ ግሩፕ በኢትዮጵያ ሰፋ ያለ ኢንቨስትመንት አድርጓል፡፡

በተለይም የመረጃና የመዝናኛ አገልግሎት ተደራሽነትን በመጨመር እንዲሁም በስፖርትና በመዝናኛ ዘርፎች ሀገራዊ ይዘት ያላቸውን ፕሮግራሞች በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!