Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ለጥገና እና ለካሣ ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ዋና የደህንነት ባለሞያ ኢ/ር ጥበቡ ተረፈ እንደገለፁት የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት በጥገና እና በካሣ ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶበታል።
በዘርፉ የትራንስፖርት አገልግሎት እና መሠረተ ልማት ደህንነት ላይ የሚያተኩር ውይይት በአዳማ ተካሂዷል።

በመሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ስርቆት፣ ውድመት እና የባቡር አደጋዎች በውይይቱ እንደ ተግዳሮት ተነስተዋል።
የትራንስፖርት ሚንስትር ዴኤታ አወል ወግሪስ ባለፉት 3 ዓመታት 163 ጊዜያት ያህል፤ ከ652 በላይ ሰዓታት ባቡሮቹ እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉን ገልፀዋል።
በ875 እንስሳት ላይ ጉዳት፣ 961 ጊዜ ስርቆት እና የንብረት ውድመት ማጋጠሙን፣ የ27 ሰዎች ሞት እና የ11 ሰዎች የአካል ጉዳት መመዝገቡን ተናግረዋል።
በስርቆት እና በውድመት ብቻ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱንም ኢ/ር ጥበቡ ጠቁመዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.