Fana: At a Speed of Life!

15ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በምክር ቤቱ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት፣ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት “እኩልነትና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና’’ በሚል መሪ ቃል የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተከብሯል፡፡
በአሉን አስመልክተው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ እጸገነት መንግስቱ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
በንግግራቸውም ከሃዲው የህውሃት ቡድን በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በሚገኙ ዜጎች ላይ ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋ ማድረጉ ሳያንስ የህዝብ አለኝታ በሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጥቃት መፈጸሙን ገልጸው÷ በኢትዮጵያውያን እና በህዝቦቿ ላይ በይፋ የከፈተውን ጦርነት በአስደናቂ ችሎታና ወታደራዊ ጥበብ የተጠናቀቀበት ወቅት ላይ የሚከበር በአል መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ይህ የጥፋት ሃይል ሃገሪቷ የጀመረችውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለመግታትና በሕዝብና በመንግስት መካከል ያለመተማመን ተፈጥሮ ዜጎች በለወጡ ሂደት ተስፋቸው እንዲጨልም ለማድረግ ሌት ከቀን ሲሰራ መቆየቱን ምክትል አፈ-ጉባኤዋ አስታውሰዋል ፡፡
አያይዘውም የመድረኩ አላማም የህውሃት ቡድን የሄደበትን አፍራሽ መንገድና መንግስት የተጓዘበትን ትዕግስት አስጨራሽ የሰላም መንገድ ለባለድርሻ አካላት እና ለሁሉም የሃገራችን ህዝቦች በከሃዲው ቡድን ላይ የተወሰደው እርምጃ ህገ መንግስትና ህገመንግስታዊ ስርአቱን የማዳን ተግባር እንደሆነ ለማስገንዘብ እንደሆነም ወይዘሮ ዕጸገነት አብራርተዋል፡፡
በፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ-መንግስትና የፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሃይለየሱስ ታዬ በኩል በቀረቡና ሃገራዊ ለውጡን በሚመለከት ሶስት ታላላቅ ሃገራዊ የሪፎርም አጀንዳዎች ባሏቸው ሀገረ መንግስት፣ ብሔረ-መንግስት እና የዴሞክራሲ ባህል ግንባታዎችን ለማሳካት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.