በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሀይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኙ ተማሪዎች በጥሩ ደህንነት ላይ መሆናቸውን ተናገሩ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሀይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኙ ተማሪዎች በጥሩ ደህንነት ላይ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡
ተማሪዎቹ በአሁኑ ሰዓት የትምህርት አገልግሎት ቢቋረጥም በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በሀይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአሁኑ ሰዓት የህክምና እና ተመራቂ የጤና ሳይንስ ተማረዎች ይገኛሉ፡፡
ከዚህ ባሻገር በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ስፔሻላይዝድ ለማድረግ የገቡ የህክምና ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን÷ አሁን ላይ ሁሉም በሆስፒታሉ ግቢ እንዳሉም ነው የተናገሩት፡፡
ከዚህ ቀደም ከግቢው ውጪ ይኖሩ የነበሩ የስፔሻሊቲና ሰብ ስፔሻሊቲ ተማሪዎች ወደ ግቢ ገብተው የመኝታ ክፍል አግኝተው በጥሩ ደህንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው በቂ የውሃና የመብራት አቅርቦት እንደሌለም ነው ተማሪዎቹ የገለጹት፡፡
በሀይለሚካኤል ዴቢሳ