ስፓርት

7ኛው የ 30 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በቢሾፍቱ ተካሄደ

By Abrham Fekede

December 06, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 7ኛው የ 30 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሄደ፡፡

በውድድሩ በወንዶች አትሌት ኃይለማርያም ኪሮስ ሲያሸንፍ ዴሬሳ ገለታ እና ሙስጠፋ ከድር ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

በሴቶች ገበያነሽ አየለ በአንደኛነት ስታጠናቅቅ ብርሃን ምህረቱና ንግስት ሙሉነህ ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል፡፡

ይህ የጎዳና ላይ ሩጫ ከኮቪድ ወዲህ የተካሄደ የመጀመሪያው ውድድር ነው።

በውድድሩ ለሚሳተፉ አትሌቶች ነጻ የኮቪድ ምርመራ ተደርጎ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው በህክምና የተረጋገጠላቸው አትሌቶች ብቻ ተሳታፊ ሆነዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!