Fana: At a Speed of Life!

3ተኛው ሀገር ዓቀፍ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሦስተኛው ሀገር ዓቀፍ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

ሀገር ዓቀፉ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን  “ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን” በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው፡፡

በዚሁ ወቅት የትራንስፖርት ሚንስቴር ሚንስትር ወይዘሮ ዳግማዊ ሞገስ በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው መድረክ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም የህዳር ወር ቆሻሻን የማስወገድ የቆየ ልማዳችንን በየአካባቢያን በመተግበር መንገዶቻችንን እና ከተሞቻችንን ለእግረኞችና ለሳይክል ተጠቃሚዎች ንጹሕ ተረፈ ምርቶች በየቦታው እንዳይገኙ  በማድረግ ተጠቃሚው ለትራፊክ አደጋ እንዳይጋለጥ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ወይዘሮ ዳግማዊት በቀጣይም ዓመቱን ሙሉ ወር በገባ በመጨረሻው እሁድ በሚከናወነዉ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን የንቅናቄው አካል በመሆን በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰተውን በትራፊክ አደጋ የሚደርሰዉን ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመትን በጋራ ለመካላከል አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂን በመተግበር  የሳይክልና የእግረኞች መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፍትና የህብረተሰቡ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።

በዕለቱ በትራፊክ አደጋ ምክንያ ውድ ህይወታቸዉን ላጡ ወገኖች የህሊና ጸሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን የእግር ጉዞ በማድረግ፣ በብሔራዊ መዝሙር፣  በህጻናት መዝሙር እና በበርካታ ብስክሌተኞች እንቅስቃሴ ታጅቦና በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።

በመጨረሻም በመላው የኢትዮጵያ ከተሞች ይህንን ፕሮግራም በተመሳሳይ ሰዓት ያካሄዱ ዜጎችን ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.