Fana: At a Speed of Life!

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዶክተር ውለታ የ2020 የዌብ ሰሚት ዓለም አቀፍ ውድድር አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የላሊበላ ኔትወርክ መስራች ዶክተር ውለታ ለማ ፖርቹጋል በተካሄደው የ2020 የዌብ ሰሚት ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ አሸናፉ፡፡

በጤናው ዘርፍ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ28 ዓመታት ልምድ ያካበቱት ዶክተር ውለታ ከሽልማቱ በኋላ ይህ ድል የኔ ብቻ አይደለም በመላው አፍሪካ ለሚገኙ እናቶችና ህጻናት ጭምር ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ በተከሰተበት ወቅት እንዲህ ያለ ሽልማት ማሸነፍ የተለየ ነው ብለዋል፡፡

ላሊበላ ግሎባል ኔትወርክ የጤና ዘርፉን ማዘመንና ዲጂታላይዝ የሚያደርግ ተቋም ሲሆን ለ20 ዓመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ላይ መስራቱ ነው የተነገረው፡፡

ተቋሙ በአፍሪካ ያለውን የጤና ስርዓት ከማዘመን በተጨማሪ ታካሚዎችን ማዕከል በማድረግ ይሰራል እንዲሁም የጤና ሁኔታን የሚያሳዩ መረጃዎችን ይመዘግባል፡፡

መስራቿ ይህንን ሽልማት የወሰዱት ከሌሎች 700 ስራ ፈጣሪዎች ጋር ተወዳድረው ነው ተብሏል፡፡

በፖርቹጋል የተዘጋጀውና ዶክተር ውለታ ያሸነፉበት ይህ የዌብ ኮንፍረንስ በዓለም ላይ ትልቁ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.