Fana: At a Speed of Life!

በኪስማዮ ሴክተር ስድስት የ5ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አልሸባብ ጥቃት እንዳይሰነዝር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኪስማዮ ሴክተር ስድስት የተሰማራው የ5ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አልሸባብ ጥቃት እንዳይሰነዝር የሚያስችል ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ ፡፡

የሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮንን በአካባቢው የፀጥታ ጉዳይ ላይ ከሻለቃው አባላት ጋር መክረዋል።

አልሸባብ በሃገራችን እና በቀጣይ የሶማሊያ ምርጫ እንዳያደናቅፍ ቀድሞ በመረዳትና በመዘጋጀት ግዳጃችንን በተገቢው መንገድ መወጣት አለብን ብለዋል፡፡

የሻለቃው ምክርል አዛዥ ለሎጅስቲክስ ተናል ኮሎኔል አዲሱ መኮንን ሰራዊታችን ለቀጠናው ሰላም መስፈን ያለምንም መዘናጋት ጠንክሮ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል ፡፡

በቀጣይ የሚደረጉ የጁባላንድና የፌደራል መንግስት ምርጫን ለማሳለጥ ዝግጁነትን በማረጋገጥ የተቀናጀ ግዳጅ ለመወጣት እንደተዘጋጁ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴርር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.