Fana: At a Speed of Life!

በህንድ ባልታወቀ በሽታ ምክንያት በርካቶች ሆስፒታል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ምክንያት በርካታ ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ፡፡

በሃገሪቱ ደቡባዊ ግዛት አንድራ ፕራዴሽ ውስጥ ምንነቱ ባልታወቀው በሽታ ቢያንስ አንድ ሰው ለህልፈት ሲዳረግ 227 ሰዎች ሆስፒታል ገብተዋል ነው የተባለው ፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 70 ሰዎች ከሆስፒታል መውጣታቸው የተገለፀ  ሲሆን ÷ 157 የሚሆኑት ግን አሁንም በህክምና ላይ እንደሚገኙ የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል ፡፡

በሽታው በያዛቸው ሰዎች ላይ ማቅለሽለሽ  እና ራስን ስቶ መውደቅ መስተዋሉን የጤና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ሆስፒታል ለገቡት ታማሚዎች በሙሉ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገ ሲሆን÷ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የበሽታውን ምንነት ለማወቅ ምርምራ እተካሄደ መሆኑም ታውቋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.