Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደዳር ከዛላምበሣ፣ ውቅሮ፣ አዲግራት እና ዕዳጋ ሐሙስ ከተሞች ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ፡፡
በውይይቱ ነዋሪዎቹ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጎን በመሆን ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰሩ ተጠይቋል፡፡
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ኮሚቴ አባል አቶ ሃብታይ ገብረማርያም እንዳሉት÷ ውይይት በተደረገባቸው ሁሉም አካባቢዎች የመንግሥት ተቋማት ወደ ስራ ገብተው አገልግሎት እንዲሰጧቸው ጥያቄ አንስተዋል።
በተለይም የጤና ተቋማት፣ የመብራት፣ የቴሌኮምና ሌሎች የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት በአፋጣኝ ሥራ ይጀምሩልን የሚሉ ጥያቄዎች በስፋት መነሳታቸውን ተናግረዋል።
የህወሓት ጁንታ በመንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻ ከተወገደ በኋላ ሕዝቡ በፍትሃዊነት የሚያስተዳድረው አካል እንደሚፈልግ መጠየቁንም ገልጸዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ሳባ ገብረማርያም በበኩላቸው ÷ በመጪዎቹ ቀናት ቅድሚያ በከተሞች ጊዜያዊ አስተዳዳሪዎችን በማቋቋም የሕዝቡን ጥያቄዎች በሂደት እንዲፈቱ የሚሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ህዝቡን በማወያየት ላይ እንደሚገኙ ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.